+ All Categories
Home > Documents > Brochure aceer ok

Brochure aceer ok

Date post: 22-Jul-2016
Category:
Upload: etio-bologna
View: 239 times
Download: 3 times
Share this document with a friend
Description:
Broscure ACEER
Embed Size (px)
of 2 /2
አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች በማህበሩ አላማና ግብ ማመን፣ መተዳደሪያ ደንቡን መቀበል፤ የአመልካች ቅጽ ሞልቶ መመዝገብ መዋጮዎችን በወቅቱ መክፈል ይጠበቅበታል/ባታል፤ በማሕበሩ የእቅድ ስራዎች ላይ ተባባሪነት መሆን ወይም አስተዋጽኦ ማድረግ፤ ከኢትዮጵያውያን/ት ጋር በጋብቻና በማደጎ ትስስር ያላቸው ዜጎች ከሆኑ... ስለዚህ አባል ለመሆን ከፈለጉ ይመዝገቡ የአባልነት ምዝገባና የመዋጮ ክፍያ ከማህበሩ ዋነኛ የገቢ ምንጮች መካካል ከአባላት ምዝገባ እና ወርሃዊ መዋጮ የሚገኝ ገቢ በመሆኑ ይህንን እና ሌሎች ሁኔታዎችን በማገናዘብ የአባልነት ምዝገባ ክፍያ እና የወርሃዊ መዋጮ ተመን አውጥቷል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ግለሰብ የማህበሩ አባል ለመሆን መስፈርቱን ሟሟላት፣ የማመልከቻውን ቅጽ ሞልቶ መመዝገብና ክፍያውን መክፈል ይኖርበታል። ይህንንም ሲያጠናቅቅ የአባልነት መታወቂያ ይሰጠዋል/ጣታል። 4 ለአባልነት መመዝገቢያ ............................. 25.00 ወርሃዊ መዋጮ ........................................... 2.00 የአመቱን በመዋጮ በአንድ ጊዜ መክፈል ይበጃል።
Transcript
Page 1: Brochure aceer ok

አባል ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

በማህበሩ አላማና ግብ ማመን፣

መተዳደሪያ ደንቡን መቀበል፤

የአመልካች ቅጽ ሞልቶ መመዝገብ

መዋጮዎችን በወቅቱ መክፈል ይጠበቅበታል/ባታል፤

በማሕበሩ የእቅድ ስራዎች ላይ ተባባሪነት መሆን

ወይም አስተዋጽኦ ማድረግ፤

ከኢትዮጵያውያን/ት ጋር በጋብቻና በማደጎ ትስስር

ያላቸው ዜጎች ከሆኑ...

ስለዚህ አባል ለመሆን ከፈለጉ ይመዝገቡ

የአባልነት ምዝገባና የመዋጮ ክፍያ

ከማህበሩ ዋነኛ የገቢ ምንጮች መካካል ከአባላት ምዝገባ እና ወርሃዊ መዋጮ የሚገኝ ገቢ በመሆኑ ይህንን እና ሌሎች ሁኔታዎችን በማገናዘብ የአባልነት ምዝገባ ክፍያ እና የወርሃዊ መዋጮ ተመን አውጥቷል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ግለሰብ የማህበሩ አባል ለመሆን መስፈርቱን ሟሟላት፣ የማመልከቻውን ቅጽ ሞልቶ መመዝገብና ክፍያውን መክፈል ይኖርበታል። ይህንንም ሲያጠናቅቅ የአባልነት መታወቂያ

ይሰጠዋል/ጣታል።

4

ለአባልነት መመዝገቢያ ............................. € 25.00

ወርሃዊ መዋጮ ........................................... € 2.00

የአመቱን በመዋጮ በአንድ ጊዜ መክፈል ይበጃል።

Page 2: Brochure aceer ok

አቋም

ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ትጽዕኖ ነፃ ነው።

በማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጣልቃ አይገባም።

ፖለቲካዊ አገልግሎት አይሰጥም።

ለየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አያግዝም/አይሰራም።

ለፖለቲካ አስተሳሰብ ድጋፍ/ተቃውሞ አያደርግም።

ከፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ግንኙነት አይኖረውም።

በሀይማኖት፣ በዘርና በጾታ ላይ ልዩነት አያደርግም።

ለማንኛውም የሃይማኖት እምነት አይወግንም።

የአባል መብት

= የመምራጥም ሆነ የመመረጥ

= ድምጽ የመስጠትና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣

= ስለማህበሩ መረጃ ጠይቆ የማግኘት፣

= ማሕበሩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የመጠቀም፤

= ለማህበሩ ዓላማ መሳካት የሚጠቅሙ ስራዎችን የመስራት ወዘተ...

መብት አላቸው።

የአባልነት ግዴታ

የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ፣ አላማ፣ መመሪያዎችና ውሳኔዎችን

ማክበር፣

በመደበኛ ስብሰባዎች ላይ መገኘት፣

መዋጮችን በወቅቱ መክፈል፣

የማህበሩን ጥቅም ማክበር/ማስከበር፣

የማህበሩን ንብረት መንከባከብ፣

የተሰጠውን/ጣትን ሃላፊነት መወጣት፣

የማሕበሩ መጠርያ “የኢትዮጵያ ባህላዊ ማህበር በኤሚሊያ ሮማኛ” ሲሆን በጣሊያንኛ ሲፃፍ “Associazione Culturale Etiope in Emilia Romagna” ነው። በአጭሩ

ሲጻፍ ደግሞ "ACEER" ነው፡፡

ማሕበሩ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 1994 ዓ.ም ተቋቋመ። በአሁኑ ወቅት ኢትየጵያውያን/ትን፣ ትውለደ ኢትዮጵያንና ከኢትዮጰያ ጋር ትስስር ላላቸው ዜጎች የኢትዮጵያን ባህልን የማስተዋወቅና ቋንቋን የማስተማር፣ ሰዎችን የማቀራረብና የተለያዩ የድጋፍ ስራ በመስራት ላይ

ይገኛል፡፡

አላማው / ተግባሩ

በጣሊያን ህግ፣ ደንብና የዜጎች እኩልነት መርህ ላይ

የተመሠረተ ህጋዊ ሰውነት ያለው ማህበራዊ ተቋም እንዲኖር፣

በባህላዊና በማህበራዊ ነክ ጉዳዮች አማካኝነት መሰባሰብና

መቀራረቢያ ድልድይ ለመሆን፤

የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ወግና ባህል ለህብረተሰብ ማስተዋወቅ፣

የጣሊያንን ባህል፣ ወግ፣ ልምድ፣ ቋንቋና ኑሮ በበለጠ

ለማወቅ፣

ወጣቶች የኪነጥበብ፣ የስፖርት ወዘተ... ችሎታቸውን

እንዲያዳብሩና ለአደባባይ እንዲበቁ ማገዝ፣

በጣሊያን የነዋሪነትና የዜግነት መብታችንን ማስከበር፣

መሰረታዊ የሆኑ መብቶቻችን ለማወቅ፣ ማሳወቅ፣

የጋራ ችግሮቻችንን በሕጋዊ መንገድ ለመፍታት ማስቻል፣

አባላት በሚደርስባቸው የውጣ ውረድ ችግሮችና ድንገተኛ አጋጣሚዎች ላይ ይርስበርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ መንፈስ

በይበልጥ እንዲኖር ማድረግ፣

1 3 2

አገልግሎቶች

በኤሚሊያ ሮማኛ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር የተለያዩ ቁርኝቶች ላላቸው የሌላ ሀገር ዜጎች ማገናኛና መዝናኛ

ፕሮግራሞች ማዘጋጀት እንዲቀራረቡ ማድረግ፣

ህጻናትን፣ ወጣቶችንም ሆነ አዋቂዎችን የሃገራቸውን ቋንቋ እና ባህል እንዲውቁ የሚያስችል ትምህርት

መስጠት፣

በአባላት የሕይወት ማለፍ አደጋ ሲያጋጥም ድጋፍ

ማድረግና ማስተባበር...

ወደ አካባቢያችን የሚመጡ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊው ህጋዊ ዶክመንት ስለሚያገኙበት ሁኔታ ምክር፣

ጥቆማና መረጃዎች መስጠት፣

በቋንቋ እጥረት ጉዳዮችን ለማስጨረስ ድጋፍ

ለሚያስፈልጋቸው የትርጉም አገልግሎትና ድጋፍ ማድረግ፣

ስራ ለሚፈልጉ አባላት ከስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች እና ግለሰቦች ጋር በማገናኘት ስራ የሚያገኙበትን ሁኔታ

ማመቻቸት፤

ከመንግስት ተቋሞች፣ ድርጅቶች፣ የሰራተኛ ማህበራት ወዘተ ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን

የሚያገኙበትን ሁኔታ ለአባላት ማመቻቸት፣

በሀገራችን በተለያዩ ወቅቶች ለሚከበሩት በዓላት

ዝግጅቶችን በማድረግ በጋራ ማክበር፣

ለአባላት የህግ አገልግሎት ድጋፍ ማድረግ፣

በአባላት ላይ ህገወጥ ተግበራትን መከላከል/መቃወም፣


Recommended